የማያረጀው ሳልማን ኻን
#Ethiopia | ዲያ ሚርዛ ኢትዮጵያዊ ኢስከመስለን ድረስ በቴሌቪዥን መስኮት በኩል ልጅነታችንን ያደመቀልን ታዋቂዋ የቦሊውድ ኮከብ ሳልማን ኻን ጋር ፊልም በምትሠራበት ወቅት ያጋጠማትን አዝናኝ ትዝታ ያገራችው ሲሆን ነገሩ ሲሆን 19 ዓመቷ እንደነበር ትገልጻለች።
ተዋናይቷ ይህንን የገለጸችው በቅርቡ በፋራህ ኻን የቪሎግ ዝግጅት ላይ እንግዳ ሆና በቀረበችበት ወቅት ሲሆን ሳልማን በወቅቱ “ወደፊት አንድ ቀን በፊልም ላይ የእናቴን ገጸ ባህሪ ይዘሽ ትተውኛለሽ” ሲል እንደቀለደባት ታስታውሳለች።
ይህ አዝናኝ ምልልስ የተፈጠረው እ.ኤ.አ. በ2002 “ቱምኮ ና ቡል ፓየንጌ” (Tumko Na Bhool Paayenge) በተሰኘውን የድርጊት ፊልም በሚሠሩበት ወቅት ነበር። ዲያ ሚርዛ እንደገለጸችው በፊልሙ ላይ የሳልማንን እናት ሆና የምትተውነው ተዋናይት በጣም ወጣት መሆኗን ተመልክታ ግርምቷን ስትገልጽ፣ ሳልማን “አትጨነቂ፣ ይህ ዕጣ ፈንታ አንቺንም ወደፊት ያጋጥምሻል” በማለት በፈገግታ ነግሯት ነበር። ምክንያቱም እሱ አያረጅም።
ይህ ፊልም በሥራ ዘመኗ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ሲሆን በ19 ዓመቷ የመጀመሪያዋን መኖሪያ ቤት ለመግዛት ያስቻላትን ክፍያ ያገኘችው ከዚሁ ፊልም መሆኑንም አክላ ገልጻለች።
በዚሁ የቪሎግ ቆይታቸው ላይ ፊልም አዘጋጇ ፋራህ ኻን፣ ዲያ ሚርዛ ዳግመኛ ከሳልማን ኻን ጋር መሥራት እንዳለባት ነገራታለች።
በተጨማሪም፣ ተዋናይቷ በወቅቱ የነበረውን የፊልም ቀረጻ ሂደት ወደ ኋላ መለስ ብላ በማስታወስ፣ ምንም ዓይነት የመቀየሪያ ክፍሎች ባልነበሩበት ሁኔታ ከዛፍ ጀርባ ልብሶቿን በመቀያየር እና ከሁለት መቶ ሺህ በላይ ሕዝብ በተሰበሰበበት ሥፍራ ቀረጻቸውን እንዴት በስኬት እንዳጠናቀቁ በማውሳት የድሮ ትዝታዋን አድሳለች።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.