የመንግስት ልማት ድርጅቶች ለሀገራዊ በጀት ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ድርሻ ለመሸፈን ማቀዳቸው ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የመንግስት ልማት ድርጅቶች በተያዘው በጀት ዓመት ለሀገራዊ በጀት ከሚጠበቀው ድርሻ ውስጥ ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ለመሸፈን ማቀዳቸው ተገለጸ።

​የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ መለሰ መና፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የ10 ወራት እቅድ አፈጻጸምን በገመገሙበት ወቅት እንዳስታወቁት፣ ድርጅቶቹ ከጥያቄ ምልክት ወጥተው ግዙፍ ውጤት በማስመዝገብ ላይ ይገኛሉ።

​ሰብሳቢው አክለውም፣ በመንግስት ልማት ድርጅቶች ውስጥ የመጣው ስር ነቀል የአስተሳሰብ ለውጥ ለዚህ ስኬት መሰረት መሆኑን ጠቅሰው፣ ተቋማቱ “ገቢ ካላመጣንና ትርፍ ካላስመዘገብን መኖር አንችልም” የሚል ጽኑ አቋም መያዛቸው የምርታማነት እድገቱ ዋና ሞተር እንደሆነ ገልጸዋል።

​በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ ሆልዲንጉ ስር የሚገኙ ተቋማት 277.49 ቢሊዮን ብር ግብር እና ቀረጥ በመክፈል የዕቅዳቸውን 111 በመቶ ማሳካት መቻላቸውን ተናግረዋል።

​በዚህም 22 የሆልዲንግሱ ተቋማት በታማኝ ግብር ከፋይነት ከገቢዎች ሚኒስቴር እውቅና ማግኘታቸው፣ ተቋማቱ ለፋይናንስ ግልጽነት እና ለሀገር ግዴታ መወጣት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ከቅዳሜ ገበያ ሰምተናል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: