የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ስራ ላይ ያዋሉትን “ጨቋኝ ሕግ” እንዲሽሩ ሂውማን ራይትስ ዎች ጥሪ አቀረበዓለም አቀፉ የሰብአዊ መ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ስራ ላይ ያዋሉትን “ጨቋኝ ሕግ” እንዲሽሩ ሂውማን ራይትስ ዎች ጥሪ አቀረበ
ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዎች “የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ” ለማካሄድ እና “ተቃውሞን ለመቅጣት ስልጣን ይሰጣል”  ያለውን በትግራይ ክልል ስራ ላይ የዋለ ህግ እንዲሻር ለክልሉ ባለስልጣናት ጥሪ አቀረበ።
የትግራይ ክልል ምክር ቤት ባለፈው ግንቦት ወር መጨረሻ ያጸደቀው  ህግ፤ “ኤርትራ ከምትከተለው አስገዳጅ የብሔራዊ አገልግሎት ጋር ምስስሎሽ ያለው ነው” ሲልም ድርጅቱ ተችቷል።
መቀመጫውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደረገው ሂውማን ራይትስ ዎች ባለፉት ሳምንታት አነጋጋሪ ሆኖ የሰነበተውን ሕግ በተመለከተ ጠንከር ያለ ጥሪ ያቀረበው ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 16፤ 2018 ባወጣው መግለጫ ነው።
የድርጅቱ የአፍሪካ ክፍል ምክትል ኃላፊ ላቴሺያ ባድር የክልሉ ባለስልጣናት “ሲቪል ሰዎችን ለውትድርና በመመልመልና የሚቃወሙትን በመቅጣት” ለቀጠለው ፖለቲካዊ ውጥረት ምላሽ መስጠት እንደማይኖርባቸው ጥሪ አቅርበዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2