የኢትዮጵያ B Boy እና B Girl የብሬክ ዳንስ ውድድር በአድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት ተካሄደ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | አዲስ አበባ — የኢትዮጵያ B Boy እና B Girl የብሬክ ዳንስ ውድድር ሰኔ 13/2018 ዓ.ም. በአድዋ ድል መታሰቢያ ፊት ለፊት በድምቀት ተካሂዷል።

ውድድሩ “Building Unity and Inclusive Opportunities Through Sport and Dialogue” በሚል መሪ ቃል ለስድስት ወራት እየተተገበረ ባለው ፕሮጀክት ሥር የተሳተፉ 45 የሚደርሱ ታዳጊ ወጣቶች ያቀረቡት የመጨረሻ የብቃት ማሳያ ነበር።

ተሳታፊዎቹ በብሬክ ዳንስ፣ በሕይወት ክህሎት እና በተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ለወራት ሲሳተፉ ቆይተዋል።

ፕሮጀክቱ በNutrition for Education and Development (N4ED) አስተባባሪነት፣ በፈረንሳይ ኤምባሲ የገንዘብ ድጋፍ እና ከሀዊ ዳንስ ኢንተርቴይመንት እና እሺ ሚዲያ ጋር በትብብር የሚተገበር ሲሆን፣ ወጣት ሴቶችን፣ ወጣት ወንዶችን እንዲሁም ከአካል ጉዳት ጋር የሚኖሩ ወጣቶችን በአንድነት በማሳተፍ ተሰጥኦና ብቃትን ለማበረታታት ያለመ ነው።

በዕለቱ ተሳታፊዎች በከተማው ታዋቂ የB Boy እና B Girl ዳኞች ተገምግመው የተመረጡ ሲሆን፣ ለአሸናፊዎችና ለተሳታፊዎች የተለያዩ ማበረታቻዎች በፕሮጀክቱ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደሚበረከቱ ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ የመዝጊያ ፕሮግራም እና የተሳታፊ ብሬክ ዳንሰኞች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት አርብ ሰኔ 19/2018 ዓ.ም. በአሊያንስ ኢትዮ-ፍራንሴስ በሚካሄደው ዝግጅት ላይ በተጋበዙ እንግዶች ፊት ይከናወናል።

በመጨረሻም አዘጋጆቹ ለዝግጅቱ መሳካት እና ለደማቁ የጎዳና ላይ ትርኢት አስፈላጊውን ድጋፍ ላደረጉ የአድዋ ድል መታሰቢያ ኃላፊዎች ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

#BreakDance #BBoy #BGirl #Ethiopia #YouthEmpowerment #N4ED #HawiDanceEntertainment #AdwaMemorial #AddisAbaba #StreetDanceCulture






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: