ባይናንስ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ባደረገው ውይይት መድረኩ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል እንደገና መሥራት ጀመረ
የዓለማችን ግዙፉ የክሪፕቶከረንሲ መለዋወጫ መድረክ ባይናንስ ከኢትዮጵያ የቁጥጥር አካላት ጋር ካደረገው ስኬታማ ውይይት በኋላ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል በድጋሚ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
ኩባንያው ማክሰኞ ዕለት ለተጠቃሚዎቹ በላከው ኢሜይል መድረኩ ክፍት መሆኑን ገልጾ፥ ላሳዩት ትዕግሥት ምስጋና አቅርቧል።
ይህ ዕድገት የመጣው ኢትዮጵያ የፋይናንስና የዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፏን ለግልና ለውጭ ኢንቨስተሮች በከፊል እየከፈተች ባለችበት ወቅት ነው።
ሆኖም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም ብር ብቸኛው ሕጋዊ መገበያያ መሆኑን በመግለጽ በክሪፕቶከረንሲ ግብይት ላይ እገዳ መጣሉ ይታወሳል።
ባይናንስ ይህ አዲስ መከፈት በኢትዮጵያ የክሪፕቶከረንሲ ፖሊሲ ላይ ለውጥ ስለማምጣቱ የሰጠው ዝርዝር ማብራሪያ ባይኖርም፥ ለኢትዮጵያውያን ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።
@Seledadotio

No comments yet.