#FastMereja I በአይሪሽ ደራሲ ኦውጉስታ ግሪጎሪ ተፅፎ በአንጋፋው ተርጓሚ ተፈሪ አለሙ ወደ አማርኛ የተቀየረው ‘አሉ’ የተሰኘው አዲስ የኮሜዲ ቴአትር በሀገር ፍቅር ቴአትር አዳራሽ ዛሬ ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ ተመርቆ ለእይታ በቃ።
ይህ በሰው ልጅ አሉባልታና ወሬኝነት ዙሪያ የሚያጠነጥነው ተውኔት፥ በታዋቂው አዘጋጅ አብዱልከሪም ጀማል እና በረዳት አዘጋጅ ኃ/ገብርኤል ደምሴ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለመድረክ በቅቷል።
በቴአትሩ ላይ ፍቃዱ ከበደ፣ አለምፀሀይ እጅጉ፣ ቅድስት ገብረስላሴ እና ትዛዙ ታዬ ያሉ የበርካታ ተወዳጅ ተዋንያን ስብስብ የተሳተፉበት ሲሆን፣ የመጀመሪያ ቀናት ዕይታውም በታዳሚው ዘንድ ከፍተኛ ሳቅና አዎንታዊ ግብረመልስ አግኝቷል።
በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ሁልጊዜም ዘውትር ሮብ የትርኢት መርሃ-ግብር መሰረት ለተመልካች መቅረቡን ይቀጥላል።



Source: FastMereja









No comments yet.