ራስ ገዝ ሊሆን የመጨረሻ ደረጃ የደረሰው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው በቅድመ ምረቃ፣ በድኅረ ምረቃ ፣ በሰብስፔሻሊቲ እና በሦሥተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 4ሺህ 83 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 30 የጎንደር ከተማ እና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በሊደርሺፕ በድህረ ምረቃ የሚመረቁ ይሆናል።

ከተመራቂ ተማሪዎች በተጨማሪ ለስምንት አንጋፋ የተቋሙ ምሁራን የሙሉ ፕሬሰርነት ማዕረግ ሲሰጥ፥

ለታዋቂው የሰው ዘር ጥናት ምሁር ለሆኑት ፕሮፌሰር ዶናልድ ካርል ጆሃንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ጉባኤ በሰው ልጅ አመጣጥ ሳይንስ ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ፣ በምርምርና በትምህርት ዘርፍ ለአለም ያበረከቱትን የዕድሜ ልክ አገልግሎት ይህንን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ሰጥቷቸዋል።

በዛሬ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ፣ የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን ጨምሮ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶችና የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች ታድመል።

የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን በምረቃ ስነስርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ይህ የምረቃ ስነስርአት ዩኒቨርስቲው ራስ ገዝ ለመሆን ያደረገው የመጨረሻ የምረቃ ስነስርአት ነው ብለዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#ጎንደርዩኒቨርስቲ
#ጌጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemesgen #Mediacommunication






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: