በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃቶች ሊፈፀሙ የሚችሉበት አዝማሚያ ስላለ ኢትዮጵያውያን ጥንቃቄ የተሞላበት እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ አሳሰበ።
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተለና ከመንግስት ጋር አስፈላጊውን ግንኙነት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።የደቡብ አፍሪካ መንግስት በስደተኞች ላይ የኃይል ጥቃቶች እንዳይደርሱ በሁሉም አካባቢዎች ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርግ አስታውሷል።
ሁሉም ጉዳዮች በህጉ መሰረት እንደሚከናወኑ እና በቀጣይም የሀገሪቱ መንግስት የፀጥታ ማስከበር ተግባሩን እንደሚያጠናክር ኤምባሲው በመግለጫው ተናግሯል።በዚህም በስደተኞች ላይ ህገ ወጥ ድርጊት እና ጥቃቶች ሊፈፀሙ የሚችሉበት ሁኔታዎች መታየታቸውን ኤምባሲው አስረድቷል።
ስለዚህም በመላው ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በስደተኞች ላይ ሊደርሱ የሚችሉ የመብት መጣስ መሰረት በማድረግ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን እንዲያደርጉ አሳስቧል።ከሚኖሩበት አካባቢ የመንግስት አካላት እና የኮሚኒቲ አደረጃጀቶች ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲያደርጉ፣መረጃዎችንም እንዲለዋወጡ እንዲሁም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
@Seledadotio

No comments yet.