አውሮፓ በሙቀት እየተቃጠለች ነው!
በአውሮፓ ምድር ላይ ከባድና አለቅጥ የናረ የሙቀት ማዕበል መከሰቱን ተከትሎ የሰዎች ሕይወት እያለፈ፣ ትምህርት ቤቶች እየተዘጉና መደበኛ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ሙሉ በሙሉ እየተስተጓጎሉ ይገኛሉ።
ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ስፔንና ጀርመንን ጨምሮ በበርካታ አገራት ሙቀቱ የከፋ ጉዳት እያደረሰ ሲሆን፤ በጀርመን የሙቀቱ መጠን 38 ዲግሪ ሴልሲየስ ደርሷል።
ይህ ከፍተኛ ሙቀት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያዎችን፣ አስፋልቶችንና የሕንፃ ግድግዳዎችን ጭምር እያቀለጠ ሲሆን፣ የባቡር ትራንስፖርት ድርጅቶችም ተጓዦች ጉዟቸውን እንዲሰርዙና የትኬት ገንዘባቸውን እንዲመልሱ እያደረጉ ነው።
ከ300 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የአውሮፓ ሕዝብ በዚህ አስከፊ ሙቀት ውስጥ እየተሰቃየ ይገኛል።
በሌላ በኩል ግን፣ በአውሮጳ የተከሰተው ከባድ የሙቀት ማዕበል ለደቡብ ኮሪያው ሳምሰንግ፣ ለቻይናው ሚዲያ እና ለጃፓኑ ሚትሱቢሺ የመሰሉ የእስያ የአየር ማቀዝቀዣ (AC) አምራች ኩባንያዎች ግዙፍ የገበያ ዕድል ፈጥሮላቸዋል ተብሏል።
@Seledadotio

No comments yet.