ካቢ ቃል ካንደበቱ ሳይወጣ 150 ቢሊዮን ብር ወደ ካዝናው ሊያስገባ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በትውልድ ሴኔጋላዊ በኑሮው ደግሞ ጣሊያናዊ የሆነው ዝነኛው የሶሻል ሚዲያ ይዘት ፈጣሪ ካቢ ላሜ በፎርብስ የ2026 ስኬታማ የዲጂታል ፈጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ 15ኛ ደረጃንይዟል።

ያለምንም ንግግር በምልክት ብቻ በሚሠራቸውና በመላው ዓለም ተደራሽ የሆኑት አጫጭር የኮሜዲ ቪዲዮዎቹ የሚታወቀው ካቢ በአሁኑ ወቅት ከ160 ሚሊዮን በላይ ተከታዮችን በማፍራት በቲክቶክ መድረክ ላይ በዓለማችን በብዛት ተከታይ ያለው ግለሰብ መሆን ችሏል።

”ምን ይደንቃል” በሚልበት ቀለል ያሉ ቪዲዮዎቹ በዓመት 9.9 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንዲያስገኝለት ከማድረጉም በላይ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ ያሉትን አጠቃላይ ተከታዮቹን ቁጥር ወደ 252.1 ሚሊዮን አሳድጎታል።

​ይህንን አስደናቂ ተደራሽነት ተከትሎ፣ በሆንግ ኮንግ የሚገኘው ‘ሪች ስፓርክል ሆልዲንግስ’ የተባለ ድርጅት ከካቢ ላሜ የምርት ስም ጋር የተያያዘውን ኩባንያ በ975 ሚሊዮን ዶላር ለመግዛት ትልቅ ስምምነት ፈጽሟል ይታወሳል ምንም እንኳን የክፍያና የርክክብ ሂደቱ ሙሉ በሙሉ ገና ባይጠናቀቅም። ይህ ታሪካዊ ክስተት ለአፍሪካውያን ትልቅ መነቃቃትን የፈጠረ ሲሆን የአፍሪካ ተወላጅ ወጣቶች በዲጂታሉ ዓለም ያላቸውን ታላቅ አቅም በተግባር ያሳየና የቪዲዮ ይዘት ፈጣሪዎች አሁን ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የሚፈስባቸው ትርፋማ ”ቱጃሮች” እየሆኑ መምጣታቸውን በግልጽ ያሳየ ሆኗል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: