ጋናዊዉ ጠንቋይ ፖርቱጋል የዘንድሮዉን የአለምዋንጫ ታሸንፋለች አለጋናዊዉ ጠንቋይ ናና ክዋኩ ቦንሳም ፖርቱጋል የዘንድሮዉን የአለ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ጋናዊዉ ጠንቋይ ፖርቱጋል የዘንድሮዉን የአለምዋንጫ ታሸንፋለች አለ
ጋናዊዉ ጠንቋይ ናና ክዋኩ ቦንሳም ፖርቱጋል የዘንድሮዉን የአለምዋንጫ እንደምታሸንፍ ተናግሯል። “ይህ የአለምዋንጫ የፖርቱጋል እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ነዉ። ያሸንፋሉ” ሲል ተንብዮአል።
ይህ ጠንቋይ ከሰሞኑ ሀገሩ ጋና ከእንግሊዝ ጋር በነበራት ጨዋታ ሃሪ ኬን ጋና ላይ ግብ እንዳያስቆጥር እረግሜዋለሁ ብሎ ፤ እንግሊዛዊዉ አጥቂም ግብ ሳያስቆጥር ወጥቶ ነበር። ከዚህ ጨዋታ በኋላ ጋናዊዉ ጠንቋይ የአለማቀፍ ሚዲያዎችን ትኩረት ስቦ ቆይቷል።
ይህ ጠንቋይ በፈረንጆቹ 2014 ክርስቲያኖ ሮናልዶን እረግሞት ነበር። በወቅቱ በነበረዉ የአለምዋንጫ ወቅትም ሮናልዶ በጉዳት ነበር የተጫወተው ይባላል። ጠንቋዩም በእኔ እርግማን ነዉ ተጨዋቹ የተጎዳዉ ብሎ ነበር።
አሁን ደግሞ የዘንድሮዉን የአለምዋንጫ ፖርቱጋል ታሸንፋለች ብሏል። ይህ ጠንቋይ በአካን ቋንቋ የስሙ ትርጓሜ “የእሮቡ ሠይጣን” እንደማለት ነዉ።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: