#FastMereja | በአሜሪካ የተመሰረተውና በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ተግባራዊ የሆነው “ስቴም ፎር ኪድስ”፣ የህፃናትን የፈጠራ ችሎታ የሚያሳድጉ የቴክኖሎጂ ትምህርቶችን እየሰጠ ይገኛል። የዚህ የትምህርት ፕሮግራም ዋና ዓላማ ለህፃናት የቴክኖሎጂ ትምህርቶችን በአዲስና በሚስብ መንገድ ማስተማር ሲሆን፣ በተለይ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና በማሽን ለርኒንግ (Machine Learning) ዘርፎች ላይ ያተኩራል።
የትምህርት ፕሮግራሙ በቴክኖሎጂ ላይ ከሚሰሩ ባለሙያዎች እና ከአካዳሚክ ሊቃውንት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ካሪኩለም እንደሚጠቀም ተገልጿል። የትምህርት አሰጣጡም በአካል በመገኘት፣ ከትምህርት ሰዓት ውጪ (After school)፣ በክረምት ካምፕ እና በኦንላይን መንገዶች እንደሚከናወን ተጠቁሟል።
ይህ የትምህርት አቀራረብ የህፃናትን የፈጠራ ችሎታ፣ በጥልቀት የመረዳት ችሎታ (Critical Thinking) እና በጋራ የመስራት ባህልን ለማሳደግ እንደሚረዳ የፕሮግራሙ አዘጋጆች ገልጸዋል።
ከ4 እስከ 18 ዓመት የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ህፃናትና ወጣቶች፣ የዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ካሪኩለም በመጠቀም ስልጠናው ይሰጣል።
እስካሁን በስልጠናው ከ5,000 በላይ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፤ በአሁኑ ዓመት ብቻ 1,500 ተማሪዎች በአዲስ አበባ በሚገኙ ማዕከላት እየሰለጠኑ ነው።
ፕሮግራሙ በአሁኑ ወቅት በአብዛኛው የግል ትምህርት ቤቶችን ተጠቃሚ እያደረገ ቢሆንም፣ ወደፊት ግን ይህን አገልግሎት ለመንግስት ትምህርት ቤቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማዳረስ እየተሰራ ነው።
በ2018 ዓ.ም. በየትምህርት ቤቱ እና ስልጠና ማዕከሎች የኮዲንግ፣ ሮቦቲክስ እና ኢንጂነሪንግ ስልጠና የወሰዱ ልጆች የዓመቱ መዝጊያ የስቴም ውድድር (STEM Competetion) ተካሂዷል።



Source: FastMereja









No comments yet.