የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን

- Advertisement -
Sidebar AD

የኢትዮጵያ አዲስ ብሔራዊ ፓርክ ሆነ

#Ethiopia | የሰሜን ሸዋ ዞን በአንኮበር፣ ባሶና ወራና እና ጣርማ በር ወረዳዎች የሚገኘው ታሪካዊው ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ በብሔራዊ ፓርክነት እንዲተዳደር በአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ጸድቋል።

ከ8,732 ሄክታር በላይ ስፋት ያለው በርካታ የእፅዋትና የእንስሳት ዝርያዎችን የያዘ የተፈጥሮ ሀብት ሲሆን፣ ወደ ብሔራዊ ፓርክነት ማደጉ ዘላቂ ጥበቃን ለማጠናከርና ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።

የአማራ ክልል የአካባቢና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን እንደገለጸው፣ ይህ ውሳኔ አካባቢውን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የኢኮ ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

ባለሥልጣኑ በአሁኑ ወቅት በክልሉ አምስት ብሔራዊ ፓርኮችና ሰባት የማኅበረሰብ ጥብቅ ስፍራዎችን እያስተዳደረ ሲሆን፣ አዲሱ የወፍ ዋሻ ብሔራዊ ፓርክም በጥበቃና በልማት ዘርፍ ተጨማሪ ትኩረት እንደሚያገኝ ገልጿል።

በተጨማሪም ለሰሜን ሸዋ ማኅበረሰብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ፣ የፓርኩ ጥበቃና ልማት እንዲሳካ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

#WofWashaNationalPark #EthiopiaTourism #AmharaRegion #LandOfOrigins #EcoTourism #GreenEthiopia #ProtectNature Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: