#Ethiopia | የምረቃ ቀን… ለብዙዎች ከዓመታት ጥረት በኋላ የሚደርስ የደስታ ጊዜ ነው። ቤተሰብ፣ ጓደኞች እና ወዳጆች ተሰባስበው “እንኳን ደስ አለህ!” የሚሉበት ልዩ ዕለት።
ነገር ግን ለአንዲት የህግ ተመራቂ፣ ይህ ቀን በደስታ ሳይሆን በሀዘን ተጀመረ።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ሁሉም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሲተቃቀፉ፣ ፎቶ ሲነሱ እና ሲደሰቱ፣ እሷ ግን ብቻዋን ነበረች። ቤተሰቦቿ ሊመጡ አልቻሉም፤ ምክንያቱ ምናልባት የአቅም ጉዳይ ሊሆን ይችላል።
ልቧ በሀዘን ተሞልቶ፣ ወደ ዶርሟ ተመልሳ እንባዋን አፈሰሰች። ከተረጋጋች በኋላም አየር ለመቀየር ወደ ከተማ ወጣች። አንድ ካፌ ውስጥ ገብታ ምግቧን በልታ፣ መጠጧን ጠጥታ በሐሳብ ተውጣ ተቀምጣ ሳለች…
በድንገት የካፌው ሙዚቃ ተቀየረ። የ”እንኳን ደስ አለሽ!” ድምፅ ተሰማ።
ግራ ተጋብታ ዞር ስትል፣ አራት የባህር ዳር ወጣቶች የ”እንኳን ደስ አለሽ” ጽሑፍ የተጻፈበትን ኬክ ከተበራ ሻማ ጋር ይዘው ወደ እሷ እየመጡ ነበር።
ያልጠበቀችው ይህ የፍቅርና የሰብአዊነት ስጦታ ልቧን በእጅጉ አነካው። እንባዋን መቆጣጠር አልቻለችም። የደስታ እንባ በጉንጮቿ ላይ ፈሰሰ።
“እስከ ዛሬ ብቻዬን ነበርኩ። የቅርብ ጓደኛ እንኳን የለኝም። የሚከፋኝ አይመስለኝም ነበር፤ ግን በዚህ ቀን በጣም ከፋኝ። አለቀስኩ። ከዚያም ይህ ሆነ…” ስትል በእንባ ደስታዋን ገለጸች።
በመጨረሻም ለእነዚያ ደግ የባህር ዳር ልጆች ከልብ ምስጋናዋን አቀረበች።
አንዳንድ ጊዜ የሰውን ልብ የሚያክም ትልቅ ስጦታ ገንዘብ ሳይሆን፣ “አንቺን አስበናል” የሚል ትንሽ የደግነት ተግባር ብቻ ነው።
#ሞገደኛው አበባው




Source: GetuTemesgen







No comments yet.