4.5 ሚሊዮን ብር ወጪ የሆነበት “ሳላያት” ፊልም ተመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja | የሮማንቲክ ኮሜዲ ዘውግ ያለው “ሳላያት” የተሰኘ አዲስ ፊልም ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዲሱ ህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት ተመረቀ፣ ከሰኔ 25፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች እንደሚታይ የፊልሙ ፕሮዲዩሰር ገልጸዋል።

​የፊልሙ ፕሮዲዩሰር እንደገለጹት፣ ፊልሙን ለመስራት እስከ ስምንት ወር የሚጠጋ ጊዜ የፈጀ ሲሆን፣ ለፊልም ስራው ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ተገልጿል፣ ፊልሙ የሮማንቲክ ኮሜዲ ዘውግ ያለው እና የህብረተሰቡን የእለተ እለት ህይወት የሚዳስስ ነው ብለዋል።

በእውነት መልቲሚዲያ ተዘጋጅቶ በሞሪያድ ኢንተርቴመንት የቀረበው ሳላያት ፊልም አለምሰገድ ተስፋዬ፣ ናታይ ጌታቸው፣ መኮንን ለአከ፣ አስቴር አለማየሁ፣ ክላራ ሙሉጌታ፣ ሊና ካሳ እና ሌሎች ተዋናዮች የተጣመሩበት ነው።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2