5ኛው ነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና ዘመቻ በደብረ ብርሃን ተጀመረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ታዝማ የውስጥ ደዌ እና የቀዶ ሕክምና ልዩ ማዕከል 5ኛውን ነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና ዘመቻ በደብረ ብርሃን ከተማ፣ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሐኪም ግዛው መታሰቢያ ሆስፒታል ማስጀመሩን አስታውቋል።

ማዕከሉ እንደገለጸው፣ ዘመቻው በተለይ በልብ ሕመም የሚሰቃዩና በአቅም ውስንነት ምክንያት የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ማግኘት ለተቸገሩ ታካሚዎች ነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና በመስጠት የሕክምና ተደራሽነትን ለማሳደግ ያለመ ነው።

ታዝማ ከዚህ ቀደም በጅግጅጋ፣ በጅማ፣ በሀዋሳ እና በወራቤ ተመሳሳይ ነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና ዘመቻዎችን በተሳካ ሁኔታ ማከናወኑንም ገልጿል።

በተጨማሪም በዘመቻው ቆይታ የተለያዩ የጤና ትምህርት መልዕክቶች እንደሚቀርቡ የገለጸ ሲሆን፣ ሕብረተሰቡ ተጨማሪ መረጃዎችን በማዕከሉ ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች እንዲከታተል ጥሪ ቀርቧል።



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1