በመጨረሻም ሌብሮን ጀምስ ሎስ አንጀለስ ሌከርስን ተሰናበተ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የቅርጫት ኳስ ታላቁ ኮከብ ሊብሮን ጀምስ የሎስ አንጀለስ ሌከርስን እንደሚለቅ አሳውቋል።

የኢኤስፒኤን (ESPN) የቅርጫት ኳስ ዘጋቢ ሻምስ ቻራኒያ ባወጣው መረጃ መሰረት ሌብሮን ጀምስ ቀጣዩን የሙያ ዘመኑን በሌላ ቡድን ለመቀጠል እንደወሰነ ገልጿል።

ሊብሮን ጀምስ ይህ ውሳኔ ከገንዘብ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ብሏል።

ጀምስ ውሳኔውን ተከትሎ በሰጠው ቃለምልልስ ለዚህ ውሳኔ የደረስኩት በገንዘብ ምክንያት አይደለም ብሏል።

አክሎም በሙያው የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ የራሱን ደስታ እና እርካታ ለማግኘት ባለው የቆየ ፍላጎት የተነሳ እንደሆነም አክሏል።

ሊብሮን በሌከርስ ቆይታው በ2020 የኤንቢኤ (NBA) የአመቱ ሻምፒዮናን ጨምሮ በርካታ ድሎችን የተጎናጸፈ ኮኮብ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ነበር።

አሁን ግን ለቀጣይ ህይወቱ የበለጠ ደስታ የሚሰጠውን አማራጭ መምረጡን ገልጿል።

ሊብሮን ጀምስ ከሌከርስ ጋር ያለው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ ቀጣይ መዳረሻው የት ይሆናል የሚለው ጥያቄ የብዙዎችን ቀልብ ስቧል።

በተለይም ጎልደን ስቴት ዋሪየርስ እና ክሊቭላንድ ካቫሊየርስ ሊብሮንን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች እንደሆኑ እየተነገረ ይገኛል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#LeBronJames #Charania
#NBAchampion #ESPNnews
#ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemsgenmediacommunication


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1