አሜሪካ ያገደችው ሶማሊያዊ የፊፋ ዳኛ በኩዌት ከፍተኛ ክብር ተቀበለ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በቅርቡ ለ2026 የዓለም ዋንጫ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ የተከለከለው ታዋቂ ሶማሊያዊ የፊፋ ዳኛ ዑመር አርታን በኩዌት ከፍተኛ ክብርና እውቅና መሰጠቱ ተገለጸ።

የኩዌት እግር ኳስ ማኅበር በሰኞ ዕለት ያበረከተው ይህ ሽልማት፣ ዳኛው በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ላሳየው ከፍተኛ ስኬትና አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት መሆኑን ገልጿል።

ከሽልማቱ በኋላ ዑመር አርታን በኩዌት ኤስሲ እና በአል ቃድሲያ ኤስሲ መካከል የተደረገውን የ2025–2026 የዛይን ፕሪሚየር ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ በዋና ዳኝነት መምራቱ ተጠቁሟል።

የኩዌት እግር ኳስ ማኅበር ሊቀመንበር ሼክ አህመድ አል-ዩሱፍ አል-ሳባህ በተገኙበት በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ፣ ኩዌት ኤስሲ ተጋጣሚውን በማሸነፍ የሊጉን ዋንጫ በኩራት አንስቷል።

የዜናው ምንጭ TRT Africa መሆኑ ተጠቁሟል።





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: