የሮማንቲክ ኮሜዲ ዘውግ ያለው “ሳላያት” ፊልም ተመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎​#Ethiopia | የሮማንቲክ ኮሜዲ ዘውግ ያለው “ሳላያት” የተሰኘ አዲስ ፊልም ትናንት ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አዲሱ ህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ቤት ተመረቀ።

ከሰኔ 25፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ሲኒማ ቤቶች እንደሚታይ የፊልሙ ፕሮዲዩሰር ገልጸዋል።

‎የፊልሙ ፕሮዲውሰር ሞገስ መኮንን እንደገለጸው፣ “ሳላያት” የተሰኘውን የሮማንቲክ ኮሜዲ ፊልም ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ለማዘጋጀት ከ4.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን ስራውም በአጠቃላይ እስከ ስምንት ወር የሚጠጋ ጊዜ ፈጅቷል።

ፊልሙ ተመልካችን እያዝናና ቁምነገር የሚያስጨብጥ ስራ መሆኑን የጠቀሰው ፕሮዲውሰሩ፣ ከሰኔ 25 ቀን ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በሚገኝ ሲኒማ ቤቶችና በክልል ከተሞች ለዕይታ እንደሚበቃ አስታውቋል።

‎በእውነት መልቲሚዲያ ተዘጋጅቶ በሞሪያድ ኢንተርቴመንት የቀረበው ሳላያት ፊልም አለምሰገድ ተስፋዬ፣ ናታይ ጌታቸው፣ መኮንን ለአከ፣ አስቴር አለማየሁ፣ ክላራ ሙሉጌታ፣ ሊና ካሳ እና ሌሎች ተዋናዮች የተጣመሩበት ነው።

‎Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ







Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2