የልጅ ሃብታሞች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በኒው ዮርክ የሚኖሩትና የሕፃንነት ጓደኛሞች የሆኑት የ21 ዓመቶቹ ሩዲ አሮራ እና ሳርታክ ዳዋን፣ የፈጠሩትን የሰው ሠራሽ ስታርትአፕ ኩባንያ ወደ ላቀ ደረጃ ካሳደጉ በኋላ የኮሌጅ ትምህርታቸውን ማቋረጣቸውን አስታውቀዋል።

ወጣቶቹ ያበለጸጉት የ-AI መማሪያ መተግበሪያ እስካሁን ባለው የሥራ ሂደት ውስጥ ከ13 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማስገኘት የቻለ ሲሆን ትምህርታቸውን ማቋረጣቸው ትክክለኛና እንዲያውም የዘገየ እርምጃ እንደነበር ቢገልጹም ይህ ነገር በቤተሰቦቻቸው እና መምህሮች እንደ ጥሩ ነገር አልተወሰደላቸውም።

ሌሎች የስራ ፈጠራ ወኪሎች ስራውን ትምህርት ሳያቋርጡ መከወን ይችሉ ነበር ብለዋል።

ስራ ፈጣሪዎቹ በሥራቸው ሂደት ውስጥ የ-AI ኮዲንግ አጠቃቀም ምርቶቻቸውን በፍጥነት ለተጠቃሚዎች ለማድረስ በእጅጉ እየረዳቸው ቢሆንም ዳዋን ግን በዚህ የቴክኖሎጂ ጥገኝነት ምክንያት የራሱ የግል የኮዲንግ ክህሎት እየቀነሰ መምጣቱን እንደሚሰማው በግልጽ አስታውቋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2