ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሶሻል ዴሞክራት ሜላት ኪሮስ ትናንት ማክሰኞ በአሜሪካ የዴንቨር አካባቢ የተካሄደውን ምርጫ አሸነፈች ። ሜላት ኪሮስ የ15 ጊዜ የአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑትን ዲያና ደጌትን ሲያሸንፉ በዴንቨር የግራ ዘመም ፖለቲከኛ ከረዥም ጊዜ በኋላ የተመዘገበ ድል ነው ተብሏል።
የ29 ዓመቷ የቀድሞ ጠበቃ ሜላት፣ የሕግ ተቋማት በእስራኤል እና ፍልስጤም ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋም የሚተች አወዛጋቢ ጽሑፍ በማኅበራዊ ገጻቸው ላይ ካጋሩ በኋላ፣ ጽሑፉን ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ከሥራቸው ተባረው ነበር።
ሜላት ኪሮስ እስራኤል በጋዛ የከፈተችውን ጦርነት « የዘር ማጥፋት » ብለው በመጥራታቸው ስማቸው ይነሳል። ።
የክልሉ የምርጫ ውጤት 78 ከመቶ ድምጽ መቆጠሩን ተከትሎ በርካታ የዜና አውታሮች የፖለቲከኛዋን አሸናፊነት ይፋ ሜላት በዲያና ደጌት ላይ የ7,000 ያህል ድምፅ ብልጫ መያዛቸው ተመላክቷል።
በሕፃንነታቸው ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ የተሰደዱት ሜላት እስራኤልን በሚደግፉ የዲሞክራቲክ ፓርቲ አባላት ላይ በሰነዘሩት ትችት እና በሚያደርጓቸው ንግግሮች “አስቀያሚ እና አስከፊ” የሚል ስም ከተሰጣቸው ሶሻሊስት የፖለቲካ ተንታኝ ሀሰን ፓይከር ጋር በፈጠሩት ጥምረት ምክንያት አወዛጋቢ ሁኔታዎች ገጥመዋቸው እንደነበር ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
ሜላት የዴሞክራቶች ደጋፊ እንደሆነ በሚነገርለት የምርጫ ክልሉ የመጭውን የህዳር ወር ጠቅላላ ምርጫ ሊያሸንፉ እንደሚችሉም ከወዲሁ ከፍተኛ ግምት አግኝተዋል።
በኒው ዮርክ ከተማም የአሜሪካ ሶሻል ዴሞክራት አባል የሆኑና የከንቲባ ዞህራን ማምዳኒ ድጋፍ የተቸራቸው ሦስት ዕጩዎች የመጀመሪያ ደረጃ ምርጫቸውን ማሸነፋቸው ይታወሳል።
DW Amharic

Source: Yeneta Tube








No comments yet.