የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመስረቅ አከማችቶ የተገኘ ግለሰብ በ6 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

- Advertisement -
Sidebar AD

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ኮተቤ ኪዳነ ምህረት አካባቢ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በመስረቅ አከማችቶ የተገኘ ግለሰብ በ6 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተፈረደበት፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ህግ ቢሮ ጋር በመተባበር ባደረጉት ኦፕሬሽን ከ3.8 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸውን የኤሌክትሪክ ኬብሎች፣ አልሙኒየሞችና መዳቦች በመስረቅ ኮተቤ ኪዳነ ምህረት አካባቢ አከማችተው የተገኙ ግለሰቦች ባሳለፍነው መጋቢት ወር መጨረሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል፡፡

በፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የካ ምድብ ችሎት 2ኛ ወንጀል ችሎት ምስክሮችን በማዳመጥ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመ ግለሰብን በ6 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

በተያያዘም በየካ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ኬብሮን መድኃኒት ቤት አካባቢ በግንባታ ላይ ከሚገኝ ህንፃ ላይ የወደቀ ህንፃ መወጣጫ ዊንች በኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኬብልና በትራንስፎርመር ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡

ከህንፃው 12ኛ ፎቅ ላይ የወደቀው ህንፃ መወጣጫ ዊንች በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ኬብል ላይ በማረፉ ከኬብሉ ጋር የተያያዘው ትራንስፎርመር የተሸከመ ኮንክሪት ፖል ከነትራንስፎርመሩ ከጥቅም ውጪ ሆኗል፡፡

ተቋሙ ጉዳት የደረሰበትን የኤሌክትሪክ ኬብልና ትራንስፎርመር በመተካት ወደ አገልግሎት ለመመለስ ከ1 ሚሊየን 9 መቶ ሺህ ብር በላይ ወጪ አድርጓል፡፡

ተቋሙ ለደረሰበት ጉዳት ካሳ ክፍያ እንዲፈፀም የምስራቅ አዲስ አበባ ሪጅን ህግ ክፍል ለየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መመሪያ ክስ መስርቷል፡፡

በፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት የካ ምድብ 2ኛ ፍ/ብሔር ችሎት በቀረበለት የፍ/ብሔር የክስ መዝገቡን ሲመለከት ቆይቶ ማስረጃዎችን ከመረመረ በኋላ ውሳኔ ሰቷል። በዚህም ጉዳት ያደረሰው ድርጅት ለተቋሙ 1 ሚሊየን 959 ሺህ 783 ብር የጉዳት ካሳ ክፍያ እንዲፈፅም ተወስኖበታል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ተከሳሽ 250 ሺህ ብር ክፍያ የፈፀመ ሲሆን ቀሪውን ክፍያ ለመፈፀም በቀጠሮ ላይ ይገኛል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1