‘Trust’ እና ‘Google TV’ የተባሉ መተግበሪያዎች የባንክ አካውንትን ለአደጋ እያጋለጡ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በኢንተርኔት ማስፈንጠሪያዎች (links) አማካይነት ወደ ስልኮች በመግባት የባንክ ሂሳብን የሚያጠፉ “Trust”፣ “Google TV” እና “Known” የተባሉ አደገኛ የአንድሮይድ መተግበሪያዎች በስፋት እየተሰራጩ መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታወቀ።

እነዚህ መተግበሪያዎች በተለይ በGoogle Chrome፣ Telegram እና WhatsApp መድረኮች ላይ የሚጋሩ ሲሆን፥ ተጠቃሚዎች ሳያውቁ የገንዘብ ዝውውር በመፈጸም ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ።

​ይህ በቴክኖሎጂ የታገዘ የሳይበር ጥቃት በስፋት እየተስተዋለ የመጣው ተጠቃሚዎች ከተላኩላቸው አጠራጣሪ ሊንኮች ላይ መተግበሪያዎቹን ሲያወርዱ መሆኑ ታውቋል። መተግበሪያዎቹ አንዴ ስልክ ላይ ከተጫኑ በኋላ ከሞባይል ባንኪንግ ጋር የተያያዙ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በመስረቅ ገንዘብ የመውሰድ አቅም እንዳላቸው ተገልጿል።

ህብረተሰቡ ከዚህ መሰሉ የሳይበር ዘረፋ ራሱን ለመጠበቅ መተግበሪያዎችን ከታመኑ ምንጮች (እንደ Play Store ወይም App Store) ብቻ ማውረድ እንዳለበት ባንኩ አሳስቧል።

​ከተጠቀሱት የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች የሚላኩ አጠራጣሪ ሊንኮችን አለመክፈት እና በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ላይ የባዮሜትሪክ (የፊት ወይም የአሻራ) እና የፒን (PIN) የደኅንነት ማረጋገጫዎችን አጣምሮ መጠቀም ለአደጋው የመጋለጥ እድልን በእጅጉ እንደሚቀንስ ተነግሯል።

#ሳይ_ቴክ


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: