🚨 እስራኤል የኢራንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የፓርላማ አፈ-ጉባኤውን ለመግደል አቅዳ ነበር” — ኒው ዮርክ ታይምስ
አሜሪካ ከኢራን ጋር እጅግ ስሱ የሆኑ ዲፕሎማሲያዊ ንግግሮችን በምታደርግበት ወቅት፣ እስራኤል የኢራኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺን እና የፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሀመድ ባቄር ቃሊባፍን ለመግደል አቅዳ እንደነበር የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል።
እንዲህ ዓይነቱ የደህንነት እርምጃ የተጀመረውን የዲፕሎማሲ ሂደት ሙሉ በሙሉ ያከሽፈዋል በሚል የሰጉት የአሜሪካ ባለስልጣናት፣ ለሁለቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጥቃት ሊሰነዘርባቸው እንደሚችል ለኢራን ሚስጥራዊ ማስጠንቀቂያ እንዲያስተላልፉ በርካታ የቀጠናውን ሀገራት ጠይቀው ነበር። በተጨማሪም ዋሽንግተን ድርድሩ በሚካሄድበት ወቅት እንዲህ ዓይነቱን ጥቃት እንዳትፈጽም እስራኤልን አጥብቃ አሳስባለች።
እስራኤል አራግቺን እና ቃሊባፍን በግድያ ኢላማ ስም ዝርዝሯ ውስጥ አስገብታቸው የነበረ ቢሆንም፣ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ውይይት ሲጀመር ግን ለጊዜው ከዝርዝሩ አንስታቸው ነበር። የአሜሪካ ባለስልጣናት እንዳሉት፣ ሁለቱ ግለሰቦች በንቁ ጦርነት ወቅት እንደ ህጋዊ ወታደራዊ ኢላማ ሊቆጠሩ የሚችሉ ቢሆንም፣ የሰላም ንግግሩ ባለፈው ሚያዝያ ከተጀመረ በኋላ ግን እነሱን መግደል ውይይቱን ሙሉ በሙሉ የሚያስቆምና ጦርነቱን በድጋሚ የሚቀሰቅስ ይሆን ነበር።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.