ልብ ጠጋኞቹ ኢትዮጵያ ገቡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ከ6 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ከ55 በላይ በጎ ፈቃደኛ የልብ ህክምና ስፔሻሊስቶች፣ ሰርጅኖችና የጤና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ህሙማን ነጻ እና ውስብስብ የልብ ህክምና ለመስጠት አዲስ አበባ ገብተዋል።

«ሄርት አታክ ኢትዮጵያ» (Heart Attack Ethiopia) በተሰኘው በጎ አድራጎት ድርጅት የተዘጋጀው 5ኛው ዙር ዘመቻ፣ በዶ/ር ተስፋዬ ተሊላ እና ዶ/ር ኦብስኔት መርዕድ የሚመራ ሲሆን፣ ከካናዳ፣ አሜሪካ፣ ሕንድ፣ ሩዋንዳ፣ ቦትስዋናና ሌሎች ሀገራት የመጡ ባለሙያዎች ከህክምና ቁሳቁሶች ጋር ወደ ሀገር ገብተዋል።

የሁለት ሳምንታት የነጻ ህክምና ዘመቻው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ በካርዲያክ ሴንተር እና በኮሪያ ሆስፒታል በአጠቃላይ በ4 የህክምና ማዕከላት ይካሄዳል። ህሙማን የሚመረጡትም በሆስፒታሎቹ ነባር የወረፋ አሰራር መሰረት መሆኑ ተገልጿል።

ድርጅቱ ባለፉት አራት ዙሮች ብቻ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ በመሸፈን 461 ታካሚዎችን ከከባድ የልብ ህመም መታደግ መቻሉን ገልጿል።

ከህክምና አገልግሎቱ በተጨማሪ 6 የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ለልዩ ስልጠና ወደ ሕንድ እንደሚላኩ የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይም በኢትዮጵያ ዘላቂ የልብ ህክምና አቅም ለመገንባት የህክምና ማዕከል ግንባታ ዕቅድ ይፋ እንደሚደረግ ተገልጿል።






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1