ዘምዘም ባንክ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ታሪክ ሰራ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ዘምዘም ባንክ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በይፋ በመመዝገብ፣ በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ውስጥ የተመዘገበ የመጀመሪያው ከወለድ ነፃ (Interest-Free) ባንክ ሆኗል።

ይህ ምዝገባ ባንኩ አክሲዮኖቹን ለህዝብ በይፋ እንዲያቀርብና በካፒታል ገበያ እንዲገበያይ የሚያስችለውን ህጋዊ ፈቃድ ያገኘበት ወሳኝ እርምጃ ነው።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መሊካ በድሪ እንደገለፁት፣ ይህ ሂደት የ15 ቢሊዮን ብር የካፒታል ግብን ለማሳካትና በካፒታል ገበያው ውስጥ ተሳትፎን ለማጠናከር ትልቅ እመርታ ነው።

የ2025/26 የፋይናንስ አፈጻጸም በአጭሩ

የደንበኞች ተቀማጭ ገንዘብ ከ11.6 ቢሊዮን ወደ 21 ቢሊዮን ብር (81% ዕድገት)

ጠቅላላ ሀብት 29.1 ቢሊዮን ብር (75% ዕድገት)

የተከፈለ ካፒታል 5.64 ቢሊዮን ብር (123% ዕድገት)

ጠቅላላ ገቢ 3 ቢሊዮን ብር

የተጣራ ትርፍ 1.8 ቢሊዮን ብር

በተጨማሪም “አንሳር ዲጂታል” አገልግሎት ከ9,800 በላይ ደንበኞችን ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ፋይናንስ ያቀረበ ሲሆን፣ ባንኩ በ130 ቅርንጫፎች ከ973,000 በላይ ደንበኞችን እያገለገለ ይገኛል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#ZamZamBank #CapitalMarket #Ethiopia #InterestFreeBank #BusinessNews




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: