እስራኤል የተኩስ አቁም ቢኖርም በደቡብ ሊባኖስ ፍንዳታዎችን እየፈጸመች ነው ተባለ

- Advertisement -
Sidebar AD

የእስራኤል ጥቃቶች የተፈጸሙት በሁለቱ ሀገራት መካከል ሰላም ለማውረድ ከሊባኖስ ባለስልጣናት ጋር ውይይት እየተደረገ ባለበት ወቅት ነው።

የእስራኤል ጦር በደቡብ ሊባኖስ አል ማንሱሪ ከተማን ማጥቃቱን እና ማጅዳል ዙን መንደር ውስጥ ፍንዳታዎችን ማድረሱን የሊባኖስ ብሔራዊ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ባለፈው ሐሙስ እስራኤል በአምቡላንስ ላይ በሰነዘረችው ጥቃት ሁለት የህክምና ባለሙያዎች የቆሰሉ ሲሆን፥ የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ድርጊቱን ‹‹ዓለም አቀፍ ሰብአዊ ህጎችን በግልጽ የጣሰ›› ነዉ ብሎታል።

እስራኤል የደህንነት ቀጣና ለመፍጠር በድንበር አቅራቢያ ያሉ ሙሉ መንደሮችን እየመታች ሲሆን፥ ውጊያው ከተጀመረ ጀምሮ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎችን ገድላ የአገሪቱን አንድ አምስተኛ ግዛት ይዛለች።

እስራኤል ዓላማዬ ሄዝቦላህን ማስቆም ነው ብትልም፥ የመብት ተሟጋቾች ግን ስልቱ ጋዛን ለኑሮ የማይመች ለማድረግ ከተሄደበት መንገድ ጋር ተመሳሳይ ነው ይላሉ።

የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሊባኖስ ፕሬዝዳንት ጆሴፍ አውን ጋር በዋይት ሃውስ ሲገናኙ ሊባኖስን ለመርዳት ቃል ገብተዋል።

እስራኤል ስለምትወጣበት የጊዜ ሰሌዳ ሲጠየቁም ‹‹በሂደት ላይ ናቸው፤ ወደ ሌላ ክፍል እየተሰማሩ ነው›› ብለዋል።

ቀጣዩ የባለስልጣናቱ ውይይት ለነሐሴ 4 በጣሊያን ተቀጥሯል።

የሄዝቦላህ መሪ ናኢም ቃሲም ስምምነቱን ‹‹ውድቅ እና ዋጋ ቢስ›› በማለት የትጥቅ ትግል ጥሪ አቅርበዋል።

ሳራ ዮሐንስ



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: