የ4 ዓመት ህጻን ልጅ በማገት 5 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ባልና ሚስት በጽኑ እስራት ተቀጡወንጀሉ የተፈፀመው ነሐሴ 12 ቀን 201…

- Advertisement -
Sidebar AD
የ4 ዓመት ህጻን ልጅ በማገት 5 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ባልና ሚስት በጽኑ እስራት ተቀጡ
ወንጀሉ የተፈፀመው ነሐሴ 12 ቀን 2017 ከጠዋቱ 3 ሰአት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ቀጠና አራት እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪ መታደል ታደሰ በ4ሺ ብር የወር ደመወዝ በቤት ሰራተኝነት በአቶ መልካሙ ረዳቴ እና በወ/ሮ ጥጋብ ጌታሁን መኖሪያ ቤት ትቀጠራለች።
ግለሰቧ በተቀጠረች በ10ኛ ቀን የቀጣሪዎቿን ወደ ስራ መሄድን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም የ4 አመት እድሜ ያለውን ህፃን ዮሴፍ መልካሙን ችብስ ልግዛልህ በማለት ይዛው ትሰወራለች።የህፃኑ ወላጆች ስራ ውለው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ልጃቸውን እና የቀጠሯትን የቤት ሰራተኛ ከቤት ያጧቸዋል።
የቤት ሰራተኛቸው የትዳር አጋር የሆነው ግለሰብ ወደህጻኑ ወላጅ አባት ስልክ በመደወል ልጅህን አግተንዋል 5 ሚሊየን ብር አምጣ ብሎ ስልኩን ይዘጋል ። የልጃቸውን መታገት ተደውሎ የተነገራቸው ወላጅ አባት እና እናትም ለአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያመለክታሉ።
ፖሊስ የቤት ሠራተኛዋ መታደል ታደሰ ከትዳር አጋሯ መሠረት አየለ ጋር በመሆን ወደ ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሀን ከተማ ጫጫ ክፍለ ከተማ ህፃኑን እንደወሰዱት ይደርስበታል።
ኋላም ተጠርጣሪዎች ቤት ተከራይተው ልጁን ካስቀመጡበት በቁጥጥር ስር በማዋል ታግቶ የነበረው ህፃን ዮሴፍ መልካሙን ከነሙሉ ጤንነቱ ለወላጆቹ አስረክቧል። የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለሚመለከተው የፍትህ አካል በመላክ ክስ እንዲመሰረት አድርጓል።
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ ጥፋተኛ ሆነው በማግኘቱ 1ኛ:- ተከሳሽ መታደል ታደሰ በ8አመት ከ4ወር 2ኛ :-ተከሳሽ መሰረት አየለ ደግሞ በ7አመት ከ9ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል ።
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2