#Grade8 የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ይፋ እንዳደረገው የዘንድሮውን የ8ኛ ክፍል ፈተና ከተፈተኑ 45,034 ተፈታኞች መካከል…

- Advertisement -
Sidebar AD
#Grade8
የሲዳማ ክልል ትምህርት ቢሮ ይፋ እንዳደረገው የዘንድሮውን የ8ኛ ክፍል ፈተና ከተፈተኑ 45,034 ተፈታኞች መካከል 29,466 (65.43%) ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ሲያልፉ 15,568 (34.57%) ተማሪዎች ፈተናውን ማለፍ አልቻሉም።
የማለፊያ ነጥብ ለመደበኛ ተማሪዎች 50% ፤ ለአካል ጉዳተኞች ደግሞ 45% መሆኑ ተገልጿል።
ከ790 አስፈታኝ ትምህርት ቤቶች መካከል 111 (14%) ትምህርት ቤቶች ሁሉንም ተማሪዎቻቸውን ሲያሳልፉ፣ 15 (1.8%) ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድም ተማሪ ማሳለፍ እንዳልቻሉ ታውቋል።
ቢሮው ” የፈተና ሂደቱ ጤናማና ከኩረጃ የፀዳ እንዲሆን በተለዩ ክላስተር ጣቢያዎች ፈተናዉ እንዲሰጥ ተደርጓል ” ብሏል።
https://sidama.ministry.et/#/result
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: