የኩሪፍቱ ባለቤት በኬንያ በምሥራቅ አፍሪካ ትልቁን የውሃ ፓርክ ሊገነቡ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የቦስተን ፓርትነርስ መስራችና የኩሪፍቱ ሪዞርትስ እና ስፓ ባለቤት የሆኑት ኢትዮጵያዊው ባለሀብት ታዲዮስ በለጠ፣ በኬንያ የቱሪዝም ዘርፍ ትልቅ ኢንቨስትመንት ለማከናወን መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል።

ባለሀብቱ በኬንያዋ የወደብ ከተማ ሞምባሳ ከአገሪቱ ባለሀብቶች ጋር በመተባበር ግዙፍ የውሃ መዝናኛ ፓርክ (Water Park) ለመገንባት ማቀዳቸውን ይፋ አድርገዋል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና ትልቁ የውሃ ፓርክ እንደሚሆን የኬንያ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ይህ የኢንቨስትመንት ዕቅድ ይፋ የሆነው፣ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ያዘጋጀውን የኢትዮጵያ የቱሪዝም መስህቦች ማስተዋወቂያ መድረክ ተከትሎ ነው።

በመድረኩ ላይ ለኬንያ ባለሀብቶች፣ ለአስጎብኝ ድርጅቶች፣ ለጋዜጠኞችና ለሶሻል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ስለ ኢትዮጵያ የቱሪዝም አቅምና የኢንቨስትመንት እድሎች ማብራሪያ ተሰጥቷል። በቀጣይም የኬንያ አስጎብኝ ድርጅቶችንና የሚዲያ ተወካዮችን ወደ ኢትዮጵያ በመጋበዝ የሀገሪቱን የቱሪዝም ሀብቶች በቀጥታ እንዲጎበኙ የማድረግ ዕቅድ መኖሩም ተገልጿል።

የታዲዮስ በለጠ ይህ አዲስ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል የቱሪዝም ትብብርን ለማጠናከር እና የምሥራቅ አፍሪካን የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ለማሳደግ ከሚደረጉ ጥረቶች መካከል አንዱ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ዋዜማ





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1