በደቡብ ወሎ ገዳም በተፈጸመው ጥቃት ፓትርያርኩ ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ ጠየቁ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳም ላይ ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. በተፈጸመው ጥቃት ጥብቅ መግለጫ አወጡ።
በጥቃቱ የመነኮሳይያት ሕይወት ማለፉን፣ በርካቶች መቁሰላቸውንና በንዋየ ቅድሳቱ ላይ ውድመት መድረሱን የገለጹት ቅዱስነታቸው፣ በዚሁ ዕለት በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአምልኮ ሥፍራ መፍረሱንና በምእመናን ላይ ጥቃት መድረሱን አውግዘዋል።
መንፈሳዊ ማዕከላት የሰላምና የእሴት ምንጭ በመሆናቸው፣ ገዳማትን መጠበቅ የባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪዎች ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል።
አሰቃቂውን ድርጊት የፈጸሙ አካላት በአስቸኳይ ለፍትሕ እንዲቀርቡ፣ ለሌሎች ገዳማት ጥበቃ እንዲደረግና ለተጎዱት ድጋፍ እንዲያገኝ ጥሪ አቅርበዋል።
በመጨረሻም ሕዝበ ክርስቲያኑ ከተጎዱት ጎን እንዲቆም አሳስበው፣ ለተበደሉት ፍትሕንና ለሀገሪቱ ሰላምን ተመኝተዋል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.