#Ethiopia | የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአመራር ደረጃ የተደረገውን ለውጥ ተከትሎ ከሰባት ዓመታት በላይ ዩኒቨርሲቲውን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ሆነው በመዛወራቸው፣ በምትካቸው አዲስ ፕሬዚዳንት መመደባቸው ታውቋል።
አዲሱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር የቻለ ከበደ ዩኒቨርሲቲው በትምህርት፣ በምርምር፣ በማኅበረሰብ አገልግሎትና በተቋማዊ አስተዳደር ያስመዘገበውን ውጤት በማስቀጠል የተሻለ አፈጻጸም ለማረጋገጥ ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብና ከሁሉም አጋር አካላት ጋር በትብብር መስራት እንደሚገባቸው ተገልጿል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማ/ሰብ ፣ የጎንደር ከተማ አስተዳደርየመንግስት ከፋተኛ ኃላዎችና የሀይማኖት አባቶች ፣ ለቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን በተቋሙ እድገት ላይ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው፣ ለአዲሱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር የቻለ ከበደ ቀጣዩ ጊዜ የተሳካ የሥራ ዘመን እዲሆን ተመኝተዋል።
ትምህርት ሚኒስተር እያደረገ ባለው አዲስ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፕሬዚዳንቶች ድልድል መሰረት የትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ-ልማት ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ በተገኙበት በዛሬው ዕለት በሁለቱም ፕሬዚዳንቶች መካከል የስራ ርክክብ ተካሂዷል።
(የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ)



Source: GetuTemesgen









No comments yet.