#Ethiopia | በመንግሥት በተገነቡ መንገዶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ አዲስ ዓመታዊ የመንገድ ግብር ለመተግበር የሕግ ረቂቅ እየተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል።
እንደ ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘገባ፣ ግብሩ ከተሽከርካሪዎች ዓመታዊ ቴክኒካል ምርመራ (ቦሎ) ጋር ተያይዞ የሚሰበሰብ ሲሆን፣ የሚከፈለው መጠንም እንደ ተሽከርካሪው ዓይነት፣ ዕድሜ እና የካርቦን ልቀት መጠን ይወሰናል ተብሏል።
በዚህ መሠረት ከፍተኛ የካርቦን ጭስ የሚያመነጩ አሮጌ ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ግብር ሊከፍሉ ሲችሉ፣ አዳዲስና ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያላቸው ተሽከርካሪዎች ደግሞ ዝቅተኛ ክፍያ እንዲፈጽሙ ይጠበቃል።
ዘገባው እንደሚያስረዳው፣ ይህ አሰራር በበርካታ አገራት ተግባራዊ ሲሆን፣ ለመንገድ ጥገናና ልማት ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመፍጠር የመንገድ መሠረተ ልማትን ለማጠናከር ያግዛል።
በተጨማሪም ግብሩ በፌዴራል፣ በክልሎች እና በከተማ አስተዳደሮች ደረጃ እንዲሰበሰብ በማድረግ የአካባቢ አስተዳደሮችን የበጀት አቅም ለማጠናከር እንደሚያስችል ተገልጿል።
ሆኖም የግብሩ መጠን፣ የአፈጻጸም ዝርዝር እና የሚጀምርበት ቀን ገና በይፋ አልተገለጸም፤ የሕግ ረቂቁ የሕግ አውጪ ሂደቱን ካጠናቀቀ በኋላ ይፋዊ መረጃ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።


Source: GetuTemesgen









No comments yet.