የትራምፕ ምስል ያረፈበትን ፓስፖርት ለዜጎች ሊሰራጭ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምስልና ፈርማ ያረፈበትን ልዩ ፓስፖርት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለህዝብ ሊያሰራጭ መሆኑን አስታወቀ።

ቀደም ሲል በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ዋናው የፓስፖርት ቢሮ ብቻ ይሰጥ የነበረው ይህ ልዩ ፓስፖርት በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ፍላጎት መታየቱ ተከትሎ ፓስፖርቱ ሊሰራጭ ነው።

በዚህም ተጨማሪ 250,000 ኮፒዎች ተዘጋጅተው በሀገሪቱ በሚገኙ 27 ዋና ዋና የፓስፖርት መስጫ ማዕከላት እንደሚሰራጩ ተገልጿል።

ፓስፖርቱ የአሜሪካን የ250ኛ ዓመት ነፃነት በዓል ለማክበር የተዘጋጀ ሲሆን የሀገር ወዳድ ፓስፖርት የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።

ዶናልድ ትራምፕ በህይወት እያሉ ምስላቸው እና የወርቅ ቀለም ፈርማቸው በስራ ላይ በሚገኝ የአሜሪካ ፓስፖርት ላይ ያረፈ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ሆነዋል።

መደበኛውን ፓስፖርት መያዝ የሚፈልጉ ዜጎች በፖስታ ቤት በኦንላይን ወይም በመደበኛ ቀናት በማመልከት ነባሩን ፓስፖርት ማግኘት እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ፓስፖርቱ ከትራምፕ ምስልና ፊርማ በተጨማሪ የአሜሪካ የነፃነት ሰነድ በውስጡ አካቷል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#America #passport
#DonaldTrump


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: