#FastMereja | የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት እና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የባህል፣ ኪነ-ጥበብና ዝክረ ታሪክ ጽህፈት ቤት በባህል፣ ኪነ-ጥበብ እና ታሪክ ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ታሪካዊ የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በታሪካዊው ሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ተፈራርመዋል።
ይህ አዲስ የትብብር ስምምነት ቀደም ሲል በባለሙያዎች ደረጃ በተናጠል ይደረጉ የነበሩ የቴአትርና ሙዚቃ ዝግጅቶችን ወደ ተደራጀና ተቋማዊ አጋርነት የሚያሸጋግር ሲሆን፣ ሀገራዊ የታሪክና የባህል እሴቶችን ለአዲሱ ትውልድ በተሻለ ጥራትና ተደራሽነት ለማስተላለፍ ያለመ ነው ተብሏል።
የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ተደራሽነቱን ለማስፋትና ህዝባዊነቱን ለማፅናት ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት ጋር የሚደርጋቸው ስትራቴጂካዊ ጥረቶች አካል የሆነው ይህ ስምምነት ከተፈረመ በኋላ፣ በአማራ ክልል ባህል ኪነ-ጥበብና ዝክረ ታሪክ ጽህፈት ቤት የተዘጋጀው “እንዛታ” የተሰኘው ትውፊታዊ ቴአትር ጥሪ ለተደረገላቸው የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችና እንግዶች ቀርቧል።



Source: FastMereja









No comments yet.