የኢትዮ-ቻይና የንግድ ግንኙነት በሕግ ማዕቀፍ እንዲቃኝ የሚያስችል ውይይት ተደረገ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​የአገር ውስጥ እና የውጪ ባለሀብቶች ያለመፈራራት እና በሕግ የተጠበቀ ጠንካራ የንግድ ትስስር እንዲፈጥሩ በማለም የተዘጋጀው ሁለተኛው የከፍተኛ ደረጃ የቻይና ኢንቨስትመንት ልዑክ ጉብኝት እና የኢትዮ-ቻይና የንግድና ኢንቨስትመንት የቢዝነስ ቱ ቢዝነስ ግንኙነት መድረክ ተካሄደ።

‎በማኩታ የሕግ አገልግሎት ኃላፊነቱ የተወሰነ የሽርክና ማህበር ማኔጂንግ ፓርትነር እና የሕግ ባለሙያ የሆኑት ወይዘሮ መሠረት ስዩም እንደገለጹት፤ መድረኩ የሁለቱን አገራት ባለሀብቶች በማገናኘት በኩል የጎላ ሚና ቢኖረውም፣ ከሁሉም በላይ ግንኙነቱ ጤናማ እና አስተማማኝ የሕግ ጥበቃ የተደረገለት እንዲሆን ማድረግ ላይ ትኩረት አድርጎ ተንቀሳቅሷል።

‎​በዚህ ታላቅ መርሃ ግብር ከኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ስታቲስቲክስ እና በቀጥታ ከተጋበዙት ጋር በመሆን እስከ አሁን ድረስ ከሃምሳ በላይ የሚሆኑ ኩባንያዎች መመዝገባቸው ተረጋግጧል።

‎አዲስ ወደ ኢንቨስትመንት መስመር እየገባች ባለች አገር ውስጥ ቴክኖሎጂን ብቻ ተማምኖ መጓዝ አደጋ ሊኖረው እንደሚችል የጠቆሙት ወይዘሮ መሠረት ስዩም፣ ባለሀብቶቹ በአካል ተገናኝተው መወያየታቸው እና የኩባንያዎችን የጀርባ ታሪክ በሕግ አግባብ ማጥናት መቻሉ የመከዳዳት እድሎችን እንደሚያስቀር አስገንዝበዋል።

‎​ማኩታ የሕግ አገልግሎት ከቻይና ጂንግሻን ማይኒንግ ኤንድ ሰፕላይ ቼይን ቴክኖሎጂ፣ ከቻይና ኮሜርሻል ስቶክ ኢንተርፕራይዞች ኢኮኖሚክ ጆይንት ኮሚቴ፣ ከዘመናዊ አገልግሎት ኢንዱስትሪ የሥራ ኮሚቴ እና ከሲሲሲ ኢን ዋን ቤጂንግ ቴክኖሎጂ ጋር በጋራ በመሆን ባዘጋጀው በዚህ መርሃ ግብር ላይ፤ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ተወካዮች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የንግድ ምክር ቤቶች እና ታዋቂ የዘርፍ ማህበራት ተሳታፊ ሆናለዋል።

‎​ይህ ትብብር ለንግድ ማህበረሰቡ ሰፊ የገበያ እድል ከመፍጠሩም በላይ፣ የሁለቱን አገራት የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የኢኮኖሚ ትስስር የሚያጠናክር ነው። ከዚህም አልፎ የሀገር ውስጥ የሕግ ባለሙያዎች በኮርፖሬት ሕግ ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ በማሳደግ የውል ዝግጅት እና የሕግ ምክር አገልግሎት ስራዎችን እንዲያገኙ ሰፊ በር የሚከፍት መሆኑ ተገልጿል።

‎ከቻይና ውጪም በዱባይ እና በሌሎች ዓለም አቀፍ ማዕከላት ተመሳሳይ ስራዎችን በመስራት የኢትዮጵያን የሕግ ማዕቀፍ እና የኢንቨስትመንት አማራጮች የማስተዋወቅ እና ሕጋዊነትን የማስፈን ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማኩታ የሕግ አገልግሎት አስታውቋል።

‎ጌትነት ተመስገን
‎Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ#MakutaLaw #EthiopiaInvestment #LegalCompliance #B2BNetworking #ChineseInvestors #CorporateLaw #InvestmentInEthiopia







Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: