#Ethiopia | በፈረንሳይ በፍጥነት እየተዛመተ የሚገኘው የሰደድ እሳት በዝነኞቹ ቤት አደጋ መደቀኑ ተነገረ።
በፈረንሳይ የተነሳውና በፍጥነት እየተስፋፋ ያለው ከፍተኛ የሰደድ እሳት የሆሊዉድ ዝነኞች አንጀሊና ጆሊ እና ብራድ ፒት የጋራ ሀብታቸው ወደ ሆነው ሻቶ ሚራቨል መኖሪያ ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኗል።
የሰደድ እሳቱ አካል የሆነው ጥቁር ጢስ ወደ 164 ሚሊዮን ዶላር በሚገመተው የሻቶ ሚራቫል ግቢ እና የወይን እርሻ ቦታ አቅራቢያ እየተቃረበ ይገኛል ተብሏል።
የእሳት አደጋ ሰራተኞች በግቢው ውስጥ የሚገኘውን የሰው ሰራሽ ሐይቅ ውሃ በመጠቀም እሳቱን ለመቆጣጠር በስፋት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙም ነው የተነገረው።
አንጀሊና ጆሊና ብራድ ፒት በዚህ መኖሪያ ቤት ከተጋቡበት ከ2014 እስከ ተለያዩበት 2021 ድረስ አብረው ኖረውበታል።
በ2021 አንጀሊና ጆሊ ድርሻዋን ለሦስተኛ ወገን ከሸጠች በኋላ በሁለቱ መካከል የተነሳው የባለቤትነት መብት ጋር በተያያዘ የተፈጠረው የህግ ውዝግብ እስካሁን ድረስ መቋጫ አላገኘም።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#France #AngelinaJolie
#BradPitt #wildfires
Source: GetuTemesgen









No comments yet.