በ2018 ዓ.ም. እስካሁን ከ6.5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል፤ በአንድ ቀን 805.3 ሚሊዮን ችግኞች ተተከሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

#Ethiopia | አዲስ አበባ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመላው ኢትዮጵያ የተካሄደው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በታሪካዊ ስኬት መጠናቀቁን ገልጸው፣ በአንድ ቀን ብቻ 805.3 ሚሊዮን ችግኞች በመተከላቸው ኢትዮጵያ አዲስ ታሪክ ማስመዝገቧን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የማጠቃለያ መልዕክት፣ ከ26 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ምንም ዓይነት ክፍያ ሳይጠይቁ እና አብዛኞቹ በዝናብ ውስጥ ቀኑን ሙሉ በመሳተፍ የችግኝ ተከላውን ማሳካታቸው የሕዝብ አንድነትና ቁርጠኝነት የሚያሳይ ታላቅ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

“ይህ በቀላሉ የሚፈጸም ሥራ አይደለም፤ የሕዝባችን ቁርጠኝነትና ሀገራዊ ኃላፊነት የታየበት ታሪካዊ እንቅስቃሴ ነው” ሲሉም አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ በተለይም ያለ ምንም ክፍያ በፈቃደኝነት በመሳተፍ ለመርሃ ግብሩ ስኬት አስተዋፅኦ ያደረጉ ዜጎችን ከልብ አመስግነዋል።

በመልዕክታቸው መሠረት፣ በ2018 ዓ.ም. እስካሁን ከ6.5 ቢሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ገልጸው፣ የቀሩት 1.5 ቢሊዮን ችግኞችም በቀሪዎቹ ወራት ተተክለው የዓመቱ 8 ቢሊዮን ችግኝ የመትከል ግብ እንደሚሳካ መተማመናቸውን ገልጸዋል።

በመጨረሻም፣ የዛሬው የችግኝ ተከላ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና ለቀጣይ ትውልድ አረንጓዴ ኢትዮጵያን ለማስረከብ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ በማስገንዘብ፣ “በአንድነት ቆመን ለነገው ትውልድ ተስፋን ተክለናል” ሲሉ መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: