“ንጹሕ አየር እና ታዳሽ ኃይል የኢትዮጵያ ዕድገት ተስፋ ዋነኛ ናቸው” – ኢንጂነር ጌቱ ገረመው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት «ተስፋን እንትከል» በሚል አገራዊ መሪ ቃል ዛሬ ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደውና 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል በተዘጋጀው ታሪካዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ላይ በንቃት በመሳተፍ አገራዊ ጥሪውን ተወጥቷል።

በዚሁ ሕዝባዊና አገራዊ ጥረት ላይ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው፣ የዋናው መሥሪያ ቤት፣ የአዲስ አበባ እንዲሁም የሸገር ሪጅኖች የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በአንድነት በመሆን በኢይሲቲ ፓርክ (ICT Park) ድልድይ ማዶ በተዘጋጀው ቦታ በመገኘት ችግኞችን በመትከል አሻራቸውን አኑረዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው በዚህ ወቅት፤ የአረንጓዴ ልማት የአካባቢን ተፈጥሯዊ ሚዛን ለመጠበቅ ብቻ ሳይሆን፣ የውኃ ሀብትና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው አክለውም “ንጹሕ አየር እና ታዳሽ ኃይል የኢትዮጵያ ዕድገት ተስፋ ዋነኛ ምሰሶ ናቸው” ብለዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ ተከላው በተመሳሳይ በሁሉም የተቋሙ ሪጅኖችና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በከፍተኛ ተሳትፎና ንቅናቄ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

#የአረንጓዴአሻራ
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
#ተስፋንእንትከል
#አረንጓዴኢትዮጵያ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: