በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 672 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 672 ኢትዮያውያን በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 8 ዙር በረራ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ከተመላሾቹ መካከል 1 ሺህ 670 ወንዶች፣ 1 ሴት፣ 1 ጨቅላ ሕፃን እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 34 ታዳጊዎች ይገኙበታል።
መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም. በተጀመረው በዚህ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ዘመቻ እስካሁን ከ90 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል፣ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለማበረታታት እየሠራ ይገኛል።
በተጨማሪም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሾች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማቀላቀል ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.