በፋብሪካ የሚመረቱ አልኮሎችና ትንባሆ ላይ የኤክሳይዝ ታክስ መጣል የምርቶቹን ዋጋ አንዲጨምር በማድረጉ የምርቶቹ የተጠቃሚዎች ቁጥር መቀነሱን ጥናት አሳየ፡፡
በሌላ በኩል ግን ጠጅ ፣ ጠላ ፣ አረቄ የመሳሰሉት ምርቶች ተጠቃሚያቸው መብዛቱን በጥናቱ ግኝት ተጠቅሷል፡፡
ጥናቱን ያጠናው በጤናው መስክ ጥናትና ምርምሮችን የሚያካሂደው ፍኖት የተሰኘ ድርጅት ነው ።
ድርጅቱ ይህን ጥናት ይፋ ያደረገው ከስድስት ዓመት በፊት በአልኮል እና በትንባሆ ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ ምን ውጤት እንዳመጣ በአማራ፣ኦሮሚያና በአዲስ አበባ ላይ ያካሄደው ዳሰሳዊ ጥናት ነው ።
በአልኮልና በትንባሆ ምርቶች ላይ የተጣለው ኤክሳይዝ ታክስ የተጠቃሚዎችን ቁጥር ከ10 እስከ 20 በመቶ እንዲቀንስ አድርጓል ሲሉ በፍኖት አሶሼት የሄልዝ ኬር ፋይናንሲንግ ባለሙያና አማካሪ የሆኑት ፕሮፌሰር አስማማው አጥናፉ የጥናቱን ውጤት ጠቅሰው ነግረውናል፡፡
በሌላ በኩል መንግስት የሚያገኘው ገቢ እንዲያድግ ማስቻሉንም በጥናቱ አረጋግጠናል ይላሉ።
የፍኖት አሶሼት መስራች አባል እና የፍኖት ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዶ/ር ፅኑኤል ግርማ በበኩላቸው
እንደ ትንባሆ እና ሲጋራ ምርቶች በህገወጥ መንገድ አሁንም እየገቡ መሆኑን ነግረውናል።
በፍኖት አሶሼት የፋይናንሲንግ ም/ ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ ደዬ በፋብሪካዎች የማይመረቱ፣ የአልኮል መጠናቸውም በማይታወቁ እንደ ጠላ፣ ጠጅ እና አረቄ ያሉ መጠጦች በሰዎች ጤና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያመጡ ነው ብለዋል ።
በሌላ በኩል በህገወጥ የሚገቡ ምርቶችን መቆጣጠር እንደሚገባም ጠቁመዋል ።
Via Sheger Fm
Source: Yeneta Tube









No comments yet.