#Ethiopia | በኢትዮጵያ የእስልምና ትምህርት እና የተውሒድ ጥሪ አስተምህሮ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት ታላቁ ዓሊም ሸይኽ አህመድ ኡስማን የቀብር ሥነ ሥርዓት በአዳማ ከተማ የሙስሊሞች መካነ መቃብር ተፈጸመ።
ለረጅም ዓመታት የእስልምናን ዕውቀት በማስተማርና በርካታ ዓሊሞችን በማፍራት ለአገሪቱ የእስልምና ትምህርት ዕድገት ትልቅ ሚና የተጫወቱት የሸይኽ አህመድ ኡስማን ህልፈት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ሐዘንን ፈጥሯል።
እንደ ሃሩን ሚዲያ ዘገባ በአዳማ ከተማ በተፈጸመው በዚህ ሥርዓተ ቀብር ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ በርካታ ዓሊሞች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ምዕመናን በመገኘት የመጨረሻ ሽኝት አድርገውላቸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.