ጉዞ ወደ ደቡብ አሜሪካ

- Advertisement -
Sidebar AD

*ሊዮ 14ኛ በቀጣይ ጉብኝት የሚያደርጉባቸውን ሦስት ሀገራት ታውቀዋል።

#Ethiopia | የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በኅዳር ወር በደቡብ አሜሪካ አገራት ጉብኝት ያደርጋሉ።

ፖፕ ሊዮ 14ኛ በኡሩጉዋይ፣ አርጀንቲና እና ፔሩ ይፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ቫቲካን አስታውቋል።

ሊዮ 14ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከሆኑ በኋላ ወደ ደቡብ አሜሪካ ሀገራት የሚያደርጉት የመጀመሪያው ጉዟቸው ይሆናል።

በዚህም ከኅዳር 6 እስከ 17 ባሉት 12 ቀናት ውስጥ በአጠቃላይ 10 ከተሞችን የሚሸፍን ጉብኝት ይሆናል ተብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቀድሞ ስማቸው ሮበርት ፍራንሲስ ፕሬቮስት በፔሩ አገር ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል በምስዮናዊነት እና በጳጳስነት ያገለገሉ ሲሆን የዚያች አገር ሙሉ ዜግነትም እንዳላቸው ተገልጿል።

ፖፕ ሊዮ ረጅሙን የጉዞ ጊዜ በፔሩ የሚያሳልፉ ሲሆን ሊማ ቺክላዮና ኩስኮ ከተሞችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የቀድሞው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የትውልድ አገራቸው አርጀንቲናን በ12 ዓመታት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪነታቸው ወቅት መጎብኘት አልቻሉም ነበር።

አሁን የሊዮ 14ኛ የአርጀንቲና ጉብኝት በአገሪቱ ዜጎች በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል ተብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#PopeLeo #Vatican
#peru #Argentina #Uruguay


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1