* በኮንታ ዞን አዲስ የተፈጥሮ የጫካ ቡና መገኘቱን ይፋ ተደረገ
#Ethiopia | በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው በታሪካዊው ኮንታ ዞን እስከ ዛሬ በሰው እጅ ያልተነካና ተፈጥሮአዊነቱን ፍጹም ጠብቆ የቆየ አዲስ የተፈጥሮ ጫካ ቡና መገኘቱ ተበሰረ።
በኮንታ ዞን ጥቁርና ጥቅጥቅ ባለው «አሜክ ኤጄቻ» ጫካ ውስጥ የተገኘው የቡና ዘር የሀገራችንን የቡና ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የሚያስጀምር መሆኑ ተገልጿል።
ይህንን ታሪካዊ ግኝት አስመልክቶ «ቶካ ፊልም መንደር እና ኢኮ ቱሪዝም» (Konta Coffee) በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አዲሱን የጫካ ቡና ይፋ ለማድረግ “ኑ ቡና ጠጡ” የተሰኘ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪና የመርሃ ግብር ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።
ድርጅቱ አዲሱ የቡና ዘር መገኘቱ ለሀገራችን አዲስ ዓለም አቀፍ ብራንድ ይዞ የሚመጣ መሆኑን ገልጿል።
እንደ ጅማ ይርጋጨፌ እና ሐረር ሁሉ «Konta Coffee» በሚል ስም ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ ገበያ በመቅረብ የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግራል።
ያልተነካውን የኮንታ የተፈጥሮ ጫካ እና የቡና መገኛ ቦታዎችን ለዓለም በማስተዋወቅ የዘርፉን ቱሪዝም በከፍተኛ ሁኔታ ያነቃቃዋል ብሏል።
የኮንታ ብሔረሰብ የሙዚቃ አቀንቃኝና የባህል አምባሳደር አርቲስት ወንዴ ኮንታ እንዳለው “ኑ ቡና ጠጡ” የሚለው ጥሪ የቡና መጠጣት ሥነ-ሥርዓት ብቻ ሳይሆን የሰላም የፍቅር የጽኑ ጉርብትና እና የኢትዮጵያዊነት መስተጋብር ማሳያ ነው ።
ይህንን ውድ ተፈጥሮአዊ ሀብት ጠብቆ ላቆየው ማኅበረሰብ እውቅና መስጠትና ባህሉን ከኪነ ጥበብ ጋር አዋህዶ ማቅረብ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው” ሲል ተናግሯል ።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለዕይታ ያልበቁ የባህል ትውፊቶችን ለዓለም ለማስተዋወቅ ቶካ ፊልም መንደር እና ኢኮ ቱሪዝም ከኢትዮጵያ የባህል ቡድን እና ከቤራ ኢንተርቴይንመንት ጋር የጋራ የሥራ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#DiscoverEthiopia
#KontaCoffee #NuBunaTetu #EthiopianCoffee #WendeKonta

Source: GetuTemesgen









No comments yet.