የአሜሪካ ስጋትና ዝግጅት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር አዲስ የኒውክሌር ስትራቴጂ ረቂቅ እያዘጋጀ መሆኑ ተገለፀ።

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) ከቻይና ወይም ከሩሲያ ጋር ቀጠናዊ ጦርነት ቢቀሰቀስ የኒውክሌር ጦር መሳርያ ለመጠቀም ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች።

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር (ፔንታጎን) ከቻይና ወይም ከሩሲያ ጋር ቀጠናዊ ጦርነት ቢቀሰቀስ አነስተኛ ርቀት የሚሸፍኑ ነገር ግን ከፍተኛ የማጥፋት ኃይል ያላቸውን የኒውክሌር ጦር መሳርያ ጥቅም ላይ ለማዋል ዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል።

ይህ በምስጢር የተያዘው አዲስ ስትራቴጂ አሜሪካ ለዘመናት ስትከተለው የነበረውን እና የኒውክሌር መሣሪያዎችን አጠቃቀም ገደብ የሚያስቀምጠውን የፖሊሲ አቅጣጫ የሚቀይር እንደሆነ ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ምንጮች አስታውቀዋል።

አዲሱ ስትራቴጂ ከቻይና ወይም ሩሲያ ጋር የሚደረግ ቀጠናዊ ጦርነት ወደ ሙሉ የኒውክሌር እልቂት ሳይሸጋገር አነስተኛ ታክቲካል መሳሪያዎችን በስትራቴጂካዊ መንገድ ለመጠቀም ያለመ መሆኑ የአሜሪካው ሲ.ቢ.ኤስ ኒውስ የዘገበው።

በፔንታጎን የፖሊሲ ጉዳዮች ሃላፊ የሆኑት ኤልብሪጅ ኮልቢ የኒውክሌር ስትራቴጂ እንደገና የማዋቀር እና የማዘጋጀት ስራውን እየመሩ የሚገኙ ሀላፊ ናቸው

ሀላፊው እንደሚሉት ይህ የአሜሪካ እርምጃ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የጂኦፖለቲካ ውጥረት እና ከኃያላን ሀገራት ስጋት አንፃር የመከላከል አቅሟን እና የጥንቃቄ ደረጃዋን ለማሳደግ የምታደርገው ጥረት ነው ብለዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#USA #Pentagon
#Tactical #Nuclear
#Weapons #China
#Russia #strategy


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: