#Ethiopia | የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት ሆነው በቅርቡ የተመረጡት በዛሬው በዓለ ሲመታቸውን አክብረዋል።
በዚሁ ሁነት ላይ አሜሪካ ወታደራዊ ድጋፍ የሚሆን የ1 ቢሊዮን ዶላር ስጦታ አበርክታለች።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ገንዘቡ የኮሎምቢያን የደህንነት ዘርፍ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለማዘመን ይውላል ብሏል።
በተጨማሪም የሁለቱን ሀገራት ወታደራዊ ትብብር ለማጠናከር እና በጋራ የደህንነት ጉዳዮች ላይ ለመስራት የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።
አዲሱ የኮሎምቢያ የቀኝ ዘመም ፖለቲካ አራማጅ ሆነው ብቅ ያሉት ፕሬዝዳንት አቤላርዶ ዴላ ኤስፕሪኤላ የአሜሪካ ቀንደኛ ደጋፊ መሆናቸው ይነገራል።
ኮሎምቢያ ከአሜሪካ ጋር በመተባበር በሚደረገው የዕፅ ዝውውር መዋጋት እንቅስቃሴ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት እንደምትሳተፍና የአሜሪካ ኮንግረስ የቀረበውን የ1 ቢሊዮን ዶላር የበጀት ጥያቄ እንደሚያፀድቀው ይጠበቃል።
“ነብሩ”በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁት አዲሱ ፕሬዝዳንት ዴላ ኤስፕሪኤላ በበዓለ ሲመታቸው ባደረጉት ንግግር በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ የዕፅ አዘዋዋሪዎች እና ህገ ወጥ ታጣቂ ቡድኖችን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ቃል ገብተዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Colombia #Usa #president
#AbelardoDeLaEspriella
Source: GetuTemesgen








No comments yet.