#ማስጠንቀቂያ ፦ ይህ ቪዲዮ አስደንጋጭ እና ለአንዳንድ ተመልካቾች ሊረብሽ የሚችል ምስል ይዟል። ከመመልከትዎ በፊት ጥንቃቄ ያድ…

- Advertisement -
Sidebar AD
#ማስጠንቀቂያ ፦ ይህ ቪዲዮ አስደንጋጭ እና ለአንዳንድ ተመልካቾች ሊረብሽ የሚችል ምስል ይዟል። ከመመልከትዎ በፊት ጥንቃቄ ያድርጉ።
በታይላንድ ደቡባዊ ክፍል በሚገኝ ግዛት እየተካሄደ በነበረ የእግር ኳስ ውድድር ላይ አንድ እግር ኳስ ተጫዋች በመብረቅ ተመትቶ ህይወቱን አጥቷል።
ጨዋታው በከባድ ዝናብ እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው መብረቅ በሜዳው ላይ በመውረድ ተጫዋቹን የመታው።
ከአደጋው በኋላ ተመልካቾች እንዲሁም የድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች እርዳታ ቢያደርጉም፣ ወደ ሆስፒታል ቢወስዱም ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም።
ባለሥልጣናት በአደጋው ተጨማሪ 12 ሰዎች በቃጠሎ መቁሰላቸውን ገልጸዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio


Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: