በኮሬ ዞን የገዛ ባሏን የገደለችው ግለሰብ በ20 ዓመት ፅን እስራት ተቀጣች

- Advertisement -
Sidebar AD

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማለ ወረዳ ደርባ ማናና ቀበሌ ልዩ ቦታዉ ወካለ ወይም ወይዶ ተብሎ በሚጠራ ቦታ ነው የወንጀል ድርጊቱ ተፈጽሟል።

ተከሳሽ ተስፋይነሽ ዘለቀ የተባለች ሲሆን ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አከባቢ ድርጊቱን ፈጽማለች።

ተከሳሽ ከትዳር አጋሯ ሳሪያ ጋር በተነሳ አለመግባባት ምክንያት ምሽት ላይ ከቤት ወጥታ እንደተሰወረች ተገልጿል።የትዳር አጋሯም ተከሳሽን ለመፈለግ ወደ ጎረቤት ቤት ሲሄድ ወደዚያ አልመጣችም የሚል ምላሽ ያገኛል። በመቀጠልም ወደ መኖሪያ ቤቱ ተመልሶ በጓሮ በኩል ባትሪ እያበራ ሲፈልጋት ተከሳሽ ተደብቃ በነበረችበት ቦታ አጠገቧ እያለፈ እያለ ይዛዉ በነበረው ቆጮ መቁረጫ የቀኝ አንገቱን አንድ ጊዜ በመቁረጥ ህይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን የኮሬ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ሲዳሞ ማዳሞ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

ፖሊስም ተከሳሽን በቁጥጥር ስር በማዋል የክስ መዝገቧን ለአቃቤ ህግ ያቀርባል።

አቃቤ ህግም ተከሳሽ በፈፀመችው ከባድ የሰዉ ግድያ ወንጀል ክስ መስርቶ ለፍርድ ቤት ያቀርባል።

ፍርድ ቤቱም ተከሻሽ ጥፋተኛ መሆኗን በቀረበለት የክስ መዝገብ በማጣራት በ20 ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል ሲሉ ምክትል ኮማንደር ሲዳሞ ማዳሞ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

Via በሳምራዊት ስዩም
©️ዳጉ_ጆርናል #viagem



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1