ኢትዮጵያ የወርቅ እና የብር ሜዳሊያዎችን በልጆቿ አገኘች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በሴቶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አስደናቂ የበላይነት በማሳየት የመጀመሪያውን የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ ለሀገራቸው አበስረዋል።

በውድድሩ አትሌት አልማዝ ዮሐንስ ርቀቱን በ9 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ ከ81 ማይክሮሰከንድ በማጠናቀቅ አንደኛ በመውጣት የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ስታስገኝ፣ አትሌት ወሰኔ አሰፋ ደግሞ በ9 ደቂቃ ከ30 ሰከንድ ከ50 ማይክሮሰከንድ በሆነ ጊዜ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች።

በዚህም ውጤት ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው እስካሁን አጠቃላይ አንድ የወርቅ፣ ሁለት የብር እና አንድ የነሐስ ሜዳሊያዎችን ማሰብሰብ ችላለች።

ይህ በኦሪገን የተመዘገበው አንጸባራቂ ድል የሁለቱ ወጣት አትሌቶች ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገራችን አትሌቲክስ የተካካይነት ተስፋ እና ብሩህ አቅጣጫ ግልጽ ማረጋገጫ ነው።

ዛሬ በታዳጊዎች የዓለም መድረክ ደምቀው የታዩት አትሌት አልማዝ እና አትሌት ወሰኔ፣ በነገው ዕለት በሚጠብቋቸው ታላላቅ የዓለም ሻምፒዮናዎች እና ኦሎምፒክ መድረኮች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገው እንደሚያበሩ ትልቅ እምነት ተጥሎባቸዋል።

#WorldU20 #Oregon2026 #EthiopianAthletics #3000mSteeplechase #FutureChampions #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: