#Fastmereja:- ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት ድርጅቱን በበለጠ መልኩ ለማስተዋወቅ እና ለደንበኞቹ ተደራሽ ለማድረግ የታወቀችውን የፋሽን ሞዴል ሂላራ ተስፋዬን በዛሬዉ እለት የድርጅቱ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ።
በስምምነቱ ወቅት የዴማ ሆፕ ሪል እስቴት የማርኬቲንግ ማናጀር አቶ ናሆም አለማየሁ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በአራት የተለያዩ ሳይቶች ላይ ትልልቅ የመኖሪያ ህንፃ ግንባታዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዉ ድርጅቱን በጥሩ ሁኔታ ለደንበኞች ለማድረስ እና ብራንዱን የበለጠ ለማጠናከር ከፋሽን እና ሞደሊንግ ዘርፍ ስኬታማ ከሆኑ አካላት ጋርአብሮ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ ሂላራ ተስፋዬን መምረጣቸውን ገልጸዋል።
የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር ሆና የተሾመችው ሂላራ ተስፋዬ በበኩሏ፤ ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት በአጭር ጊዜ ውስጥ በታማኝነት፣ በጥራት እና በከፍተኛ ተቀባይነት የብዙዎችን እምነት ያተረፈ ድርጅት በመሆኑ የዚህ ትልቅ ተቋም የክብር አምባሳደር ሆና በመመረጧ ትልቅ ደስታ እና ክብርእንደተሰማት ተናግራለች።
ሂላራ አክላም በ2024 የዓመቱ ምርጥ Runway ሞዴል፣ በ2025 የዓመቱ ምርጥ የፋሽን ሞዴል እንዲሁም በ2026 የዓመቱ ምርጥ ሞዴል እና ተጽዕኖ ፈጣሪ በመሆን ያተረፈችውን ልምድ እና ጉልበት ሙሉ በሙሉ ለድርጅቱ ስኬት እና ብራንድ እድገት እንደምትጠቀም ገልጻለች።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የድርጅቱ ማኔጅመንት አባላት፣ የሞዴል ሂላራ ጓደኞች እና ቤተሰቦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።



Source: FastMereja








No comments yet.